ሕዝቅኤል 26:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ! 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ስለ አንቺም እንዲህ ብለው ሙሾ ያወርዳሉ፤ “ ‘በባሕር ሰዎች የሚኖሩብሽ፣ ባለዝናዋ ከተማ ሆይ፤ እንዴት ጠፋሽ! ከነዋሪዎችሽ ጋራ፣ የባሕር ላይ ኀያል ነበርሽ፤ በዚያ በሚኖሩትም ሁሉ ዘንድ የተፈራሽ ነበርሽ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፤ እንዲህም ይሉሻል፦ በባሕር የተቀመጥሽ፥ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ የከበርሽ ከተማ ሆይ! እንዴት ጠፋሽ! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ በባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ የከበርሽ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ! 参见章节 |