ሕዝቅኤል 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ አቧራቸው ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ወደ ፈረስች ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፥ ከፈረሰኞች፥ ከመንኩራኩሮች እና ከሰረገሎች ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ ዐቧራ ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደ ፈረሱ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፣ ከፈረሶቹና ከጋሪዎቹ፣ ከሠረገሎቹም ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በፈረሶቻቸው ኮቴ የሚነሣው አቧራ እንደ ደመና ሆኖ ይሸፍንሻል፤ እርሱ ወደ ቅጥር በሮችሽ በሚገባበት ጊዜ ከፈረሰኛው፥ ከሠረገላውና ከመንኰራኲሩ የሚሰማው ድምፅ ተጥሳ እንደሚገባባት ከተማ ቅጥሮችሽን ያናጋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ በትቢያ ይሸፍንሻል፤ ከሠረገላ መንኰራኵርና ከፈረሶቹ ድምፅ የተነሣም ቅጥሮችሽን ያፈርሳል፤ ወንበዴ መሣሪያውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እንዲገባ በሮችሽን ይገቡባቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል፥ ሰዎችም በተናደች ቅጥር ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኵራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ትናወጣለች። 参见章节 |