Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 25:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፤ ‘የጌታ፣ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፣ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፣ የይሁዳም ቤት ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ፣ “ዕሠይ!” ብላችኋልና፣

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለአሞናውያን፥ ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቤተ መቅደሴ እንዲረክስ በተደረገ ጊዜ፥ የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ፥ የይሁዳ ሕዝብ ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ እሰይ ብላችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለአ​ሞ​ንም ልጆች እን​ዲህ በል፦ የጌ​ታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ መቅ​ደሴ በረ​ከሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ባድማ በሆ​ነች ጊዜ፥ የይ​ሁ​ዳም ቤት በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ስለ እነ​ርሱ ደስ ብሎ​ሃ​ልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለአሞንም ልጆች እንዲህ በል፦ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ እሰይ ብለሃልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 25:3
16 交叉引用  

አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፥ እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ።


በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።


ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፦ ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ቀናቸው በደረሰ፥ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ በደረሰ፥ በተገደሉት ኃጢአተኞች


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞአብና ሴይር፦ እነሆ የይሁዳ ቤት እንደ ሌሎች ሕዝቦች ነው ብለዋልና፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ “እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል” ብሏልና፥


ጠላቴ ሆይ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ብወድቅ እነሣለሁና፤ በጨለማ ብቀመጥ ጌታ ብርሃኔ ነውና።


የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ፤ በሕዝቤም ላይ አላግጠዋል፥ በድንበራቸውም ላይ ኮርተዋል።


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች መጥተው አገሩን ይወሩ ነበር።


跟着我们:

广告


广告