ሕዝቅኤል 24:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እንድትሞቅ፥ ናስዋም እንድትግል፥ ርኩሰትዋም በውስጧ እንዲቀልጥ ዝገትዋም እንዲጠፋ ባዶዋን ፍም ላይ አስቀምጣት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ጕድፉ እንዲቀልጥ፣ ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣ መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11-12 የዝገቱ ብዛት በእሳት እንኳ ስላልለቀቀ ጥረቶች ሁሉ ከንቱ ሆነዋል። ስለዚህ ከነሐስ የተሠራውን ባዶ ብረት ድስት በፋመው ከሰል ላይ ጣደው፤ ፍም እስኪመስል ድረስ ይጋል፤ በዚህ ዐይነት ርኲሰቱ ይቀልጣል፤ ዝገቱም ይጠፋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ድስቷም እስክትፈላና እስክትሰበር ድረስ በፍሙ ላይ አኖራታለሁ፤ ርኵሰትዋም በመካከሏ እንደ ሰም ይቀልጣል፤ ዝገትዋም ይጠፋል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ትሞቅም ዘንድ ናስዋም ትግል ዘንድ ርኵሰትዋም በውስጥዋ ይቀልጥ ዘንድ ዝገትዋም ይጠፋ ዘንድ ባዶዋን በፍም ላይ አድርጋት። 参见章节 |