Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ደግሞም መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው፥ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልከዋል፥ እነሆም መጡ፤ ታጠብሽላቸው ዓይንሽን ተኳልሽ፥ ጌጥም አደረግሽ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 “ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 “ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ከሩቅ ሀገ​ርም ወደ​መጡ ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ እነ​ር​ሱም በደ​ረሱ ጊዜ ይታ​ጠ​ባሉ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይኳ​ላሉ፤ ያጌ​ጣ​ሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ደግሞ መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልካችኋል፥ እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽላቸው ዓይኖችሽንም ተኳልሽ ጌጥም አጌጥሽ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:40
13 交叉引用  

በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።


ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ።


እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የአምንዝራ ሴት ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች።


ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፥ ሽቱሽንም አበዛሽ፥ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፥ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።


አንቺም የተደመሰስሽ ሆይ! ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኩል ተኩለሽ በተቆነጀሽ ጊዜ፥ በከንቱ እራስሽን ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።


እራስዋን እንዳረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ።


ደስታዋንም ሁሉ፥ በዓላቶችዋንም፥ መባቻዎችዋንም፥ ሰንበቶችዋንም፥ የተቀደሱትንም ጉባኤዎችዋን ሁሉ አስቀራለሁ።


ለእናንተም ቢሆን ውበታችሁ ውጫዊ የሆነ፥ ሹሩባ በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና የከበረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤


እንግዲህ ሰውነትሽን ታጠቢና ሽቶ ተቀቢ፥ የክት ልብስሽንም ልበሺ፥ ከዚህ በኋላ እርሱ ገብሱን ወደሚወቃበት አውድማ ሂጂ፤ ነገር ግን እስከሚበላና እስከሚጠጣ ድረስ በፊቱ አትታዪ።


跟着我们:

广告


广告