Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በግብጽ አመነዘሩ፤ በወጣትነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ ጡቶቻቸው ተዳሰሱ፥ በዚያም የድንግልናቸው የጡቶች ጫፍ ተዳበሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብጽ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱም በወጣትነታቸው ወራት በግብጽ ሲኖሩ ክብርናቸውን አጥተው በመዋረድ አመንዝሮች ሆኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በግብጽም አመነዘሩ፥ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፥ በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:3
17 交叉引用  

አመንዝራነትዋንም እንደ ቀላል በመቁጠሩዋ ምድሪቱን አረከሰች፤ እርሷም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች።


ነገር ግን በውበትሽ ተመክተሻል፥ በስምሽም አመንዝረሻል ምንዝርናሽንም ከአላፊ አግዳሚው ሁሉ ጋር አበዛሽ።


በርኩሰቶችሽ ሁሉና በአመንዝራነትሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቁተሽም በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሺም።


እኔም፦ ከእናንተ እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት ይጣል፥ በግብጽም ጣዖታት አትርከሱ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።


እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


ሆኖም በግብጽ ምድር ያመነዘረችበትን የወጣትነትዋን ዘመን አስባ ዝሙቷን አበዛች።


ስለ ወጣትነት ጡቶችሽን ግብጻውያን ጡቶችሽን የዳበሱበትን ጊዜ የወጣትነትሽን ሴሰኝነት አሰብሽ።


ትጠጪዋለሽ፥ ትጨልጪዋለሽም፥ ገሉን ታኝኪዋለሽ፥ ጡትሽንም ትቆራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስማቸውም፦ የታላቂቱ ኦሆላ የእኅትዋም ኦሆሊባ ነበረ። የእኔም ሆኑ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም፦ ኦሆላ ሰማርያ ናት፥ ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።


እኔም በዝሙት ላረጀችው፦ አሁን ከእርሷ ጋር ያመነዝራሉ፥ እርሷም ታመነዝራለች አልሁ።


ከግብጽ ጀምሮ የነበረውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በወጣትነትዋ ጊዜ ወንዶች ከእርሷ ጋር ተኝተው ነበርና፥ የድንግልናዋንም የጡቶቿ ጫፎች ዳብሰው ነበርና፥ ፍትወታቸውንም አፍስሰውባት ነበርና።


ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።


በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ ተከትለዋቸው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕታቸውን አይሠዉም። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።


“በግብጽ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ።


“እንግዲህ አሁን ጌታን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አገልግሉት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብጽም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ጌታንም አምልኩ።


በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፤ እርሷም በምሳሌያዊ አነጋገር ሰዶምና ግብጽ የተባለችው፥ ጌታቸውም የተሰቀለባት ከተማ ናት።


跟着我们:

广告


广告