Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዝሙቷን ገለጠች፥ ዕርቃንዋንም ገለጠች፥ ነፍሴ ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርሷም ተለየች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ግልሙትናዋን በአደባባይ በፈጸመችና ዕርቃን በገለጠች ጊዜ ከእኅቷ ዘወር እንዳልሁ፣ ጠልቻት ከርሷም ዘወር አልሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርቃንዋን ወደ አደባባይ በመውጣት አመንዝራነትዋ በሰው ሁሉ ዘንድ እንዲጋለጥ አደረገች፤ እኔም እኅትዋን የተጸየፍኩትን ያኽል እርስዋንም ተጸየፍኳት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዝሙ​ቷ​ንም ገለ​ጠች፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ገለ​ጠች፤ ነፍ​ሴም ከእ​ኅቷ እንደ ተለ​የች እን​ዲሁ ነፍሴ ከእ​ር​ስዋ ተለ​የች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች፥ ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:18
20 交叉引用  

የጌታም ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥ ርስቱንም ተጸየፈ።


እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፥


የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ ወዮላቸው!


ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፥ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፥ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ።


ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን በእኔ ላይ አንሥታለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ።


ጌታም እንደዚህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ።


ኢየሩሳሌም ሆይ! ነፍሴ ከአንቺ እንዳትለይ፥ አንቺንም ባድማና ማንም የማይኖርባት ምድር እንዳላደርግሽ፥ ተግሣጽን ተቀበዪ።”


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”


ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍትወትሽ ስለ ፈሰሰ፥ ከወዳጆችሽ ጋር ባደረግሽው ዝሙት ዕርቃንሽ ስለ ተገለጠ፥ ስለ ርኩሰትሽም ጣዖታት ሁሉና ለእነርሱ ስለ ሰጠሻቸው ልጆች ደም፥


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን ስለ አሰባችሁ መተላለፋችሁም ስለ ተገለጠ ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ስለ ታየ እናንተም ስለ ታሰባችሁ፥ በእጅ ትያዛላችሁ።


እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት።


ሆኖም በግብጽ ምድር ያመነዘረችበትን የወጣትነትዋን ዘመን አስባ ዝሙቷን አበዛች።


ስለዚህ በፍትወት በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ እጅ፥ በአሦር ልጆች እጅ አሳልፌ ሰጠኋት።


የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።


በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በገላጣም ስፍራ ወንበዴ ቀምቶአልና፤ እስራኤልን በፈወስሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።


“ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፤ ተጸይፌዋለሁም፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም።


ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአል፥ ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ።


በአንድ ወር ጊዜም እኔንም ስለሰለቹኝ፥ እነርሱም ስለጠሉኝ፥ ሦስቱን እረኞች አስወገድኩ።


“ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቆጡት ጌታ አይቶ ጣላቸው።


跟着我们:

广告


广告