Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ነቢዮችዋ ጌታ ሳይናገር “ጌታ እንዲህ ይላል” እያሉ የሐሰት ራእይ በማየትና በውሸት ሟርት፥ በኖራ ይለቀልቋቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ነቢያቷም በሐሰት ራእይና በውሸት ሟርት ይህን ሁሉ ድርጊት ያድበሰብሱላቸዋል፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ይላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነቢያቱ ግድግዳን ኖራ እንደሚቀባ ሰው ይህን ሁሉ ኃጢአት ይሸፍናሉ፤ በሐሰት ራእይ አየን ይላሉ፤ የውሸት ትንቢትም ይናገራሉ፤ ይህ የልዑል እግዚአብሔር ቃል ነው ይላሉ፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ምንም ቃል አልነገርኳቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ከንቱ ነገ​ር​ንም ያዩ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ እያ​ሉም በሐ​ሰት ያም​ዋ​ር​ቱ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:28
17 交叉引用  

እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥


ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤


እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፤ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።


ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ ጌታ አልላከህም።


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ።


‘የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች አገር ላይ አይመጣም’ ብለው ትንቢት ለእናንተ ይናገሩ የነበሩ ነብዮቻችሁ ወዴት አሉ?


ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፦ የጌታን ቃል ስሙ፤


አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱን ራእይ ነገር ሲያዩልህ በሐሰትም ምዋርት ሲናገሩልህ፦ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዝዞአል፥ ይገድልም ዘንድ ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል በል።


በውስጧ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና የገደለውን እንደሚበላ አንበሳ ናቸው፤ ነፍሶችን በልተዋል፥ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ወስደዋል፤ በውስጧም ብዙዎችን መበለቶች አድርገዋል።


ነቢዮችዋ ስዶችና ከሐዲ ሰዎች ናቸው፥ ካህናቶቿ መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ አምፀዋል።


跟着我们:

广告


广告