ሕዝቅኤል 22:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በውስጧ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና የገደለውን እንደሚበላ አንበሳ ናቸው፤ ነፍሶችን በልተዋል፥ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ወስደዋል፤ በውስጧም ብዙዎችን መበለቶች አድርገዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 መሳፍንቷ እያገሣ ግዳዩን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ በውስጧ ያሤራሉ፤ ሕዝቡን ይበላሉ፤ ንብረትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ፤ ብዙዎችንም ሴቶች መበለት ያደርጋሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 መሪዎቻቸው፥ በገደሉአቸው እንስሶች ዙሪያ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ሕዝቡንም በጭካኔ ይገድላሉ፤ ገንዘብም ሆነ ሌላ ንብረት ያገኙትን ሁሉ ይወስዳሉ፤ በግድያቸውም ብዙዎችን ሴቶች ያለ ባል አስቀርተዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በመካከሏ ያሉ ነቢያት እንደ አንበሳ ያገሳሉ፤ ይነጥቃሉ፤ ፈጽመውም ይቀማሉ፤ ሰውነትንም ያጠፋሉ፤ መማለጃንም ይቀበላሉ፤ በመካከልዋም መበለቶችዋ ይበዛሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በውስጥዋ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና እንደሚናጠቅ አንበሳ አንድ ሆነው ተማማሉ፥ ነፍሶችን በልተዋል፥ ብልጥግናና ሀብትን ወስደዋል፥ በውስጥዋም መበለቶችን አብዝተዋል። 参见章节 |