Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፦ ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ቀናቸው በደረሰ፥ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ በደረሰ፥ በተገደሉት ኃጢአተኞች

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰይፍ! ሰይፍ! ሊገድል የተመዘዘ፣ ሊያጠፋ የተጠረገ፣ እንደ መብረቅ ሊያብረቀርቅ የተወለወለ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ ስለ ዐሞናውያንና ስለ ስድባቸው እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን እንዲህ ብለህ አስታውቃቸው፤ ‘አጥፊ ሰይፍ ተዘጋጅቶአል፤ ለመግደልና ለማውደም እንደ መብረቅም ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል!’

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28-29 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፦ ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፥ ቀናቸው በደረሰ፥ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ በደረሰ፥ በተገደሉት ኃጢአተኞች አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱን ራእይ ነገር ሲያዩልህ በሐሰትም ምዋርት ሲናገሩልህ፦ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዝዞአል፥ ይገድልም ዘንድ ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል በል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:28
15 交叉引用  

ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


አሦርም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፥ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻል ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።


በምድረ በዳ ባሉ በተራቈቱ ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የጌታ ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ እርሱም ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።


በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።


ከንጉሣውያን ቤተሰብ አንዱን ዘር ወስዶ ከእርሱ ቃል ኪዳን ጋር አደረገ፥ አማለውም፥ የምድሪቱንም አለቆች ወሰደ፤


ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?


ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ወደ ረባት፥ ወደ ይሁዳ፥ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ መንገድን አድርግ።


ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አላሰማብሽም፥ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ርኩሰት እነርሱም እንዲሁ እጅግ ረከሱ፤ እርሱም በደላቸውን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።


跟着我们:

广告


广告