ሕዝቅኤል 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ልብ እንዲቀልጥ፥ ብዙዎች እንዲሰናከሉ ነው፤ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ የሚገድል ሰይፍ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሎአል፥ እንዲገድልም ተጠቅልሎአል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ልብ ሁሉ ይቀልጥ ዘንድ፣ የሚወድቁትም እንዲበዙ፣ በበሮቻቸው ሁሉ፣ የግድያውን ሰይፍ አኑሬአለሁ። ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሏል፤ ለመግደልም ተመዝዟል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሕዝቤ በፍርሃት በመሞላት ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እንደ መብረቅ በሚያብለጨልጭ፥ ለመግደያ የተዘጋጀውን ሰይፍ፥ በየበራፋቸው አድርጌአለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ልባቸው እንዲቀልጥ፥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ፤ ወዮ! ያብረቀርቅ ዘንድ ተሰንግሏል፤ ይገድልም ዘንድ ተስሏል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ልባቸው እንዲቀልጥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! ያብረቀርቅ ዘንድ ተሰንግሎአል ይገድልም ዘንድ ተስሎአል። 参见章节 |