ሕዝቅኤል 20:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ከሕዝቦች መካከል ባወጣኋችሁ ጊዜ፣ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች በሰበሰብኋችሁ ጊዜ፣ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኋለሁ፤ በእናንተም መካከል ቅዱስ መሆኔን በአሕዛብ ፊት እገልጣለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ተበታትናችሁ ከነበራችሁባቸው አገሮች ሕዝቦች መካከል አውጥቼ በምሰበስባችሁ ጊዜ መልካም መዓዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኋለሁ። ሌሎች ሕዝቦች እያዩ በእናንተ መካከል ቅድስናዬን እገልጣለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 ከአሕዛብ ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ ከተበተናችሁባትም ሀገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፤ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ። 参见章节 |