Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 19:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በመንጠቆዎችም አድርገው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፥ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግመኛ እንዳይሰማ ወደ እስር ቤት አመጡት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በስናግም በመጐተት ቀፎ ውስጥ ከትተው፣ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ፣ ዳግመኛ እንዳይሰማ፣ በእስር ቤት አኖሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በመንጠቆ ይዘው በወጥመድ ጎጆ ውስጥ አኖሩት፤ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ዘንድም ወሰዱት፤ ድምፁ ዳግመኛ በእስራኤል ኰረብቶች እንዳይሰማ፥ ወደ እስር ቤት አስገቡት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው በቀፎ ውስጥ አኖ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አመ​ጡት፤ ድም​ፁም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እን​ዳ​ይ​ሰማ ወደ ግዞት ቤት አገ​ቡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በሰንሰለትም አድርገው በቀፎ ውስጥ አኖሩት ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፥ ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ አምባ አገቡት።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 19:9
11 交叉引用  

በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአካዝ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ እስረኛ በማድረግ፥ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር፥ ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።


ናቡከደነፆር ኢኮንያንን አስሮ ከነእናቱ ከሚስቶቹ፥ ባለሟሎቹ ከሆኑ ባለሥልጣኖችና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።


የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደናፆር በኢዮአቄም ላይ መጣበት፤ እርሱንም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በሰንሰለት አሰረው።


ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”


ግንቦቻቸውንም አወቀ፥ ከተሞቻቸውን አፈረሰ፥ ምድሪቱና ሞላዋ ከግሣቱ ድምፅ የተነሣ ጠፋች።


የደከሙትን አላበረታችሁም፥ የታመመውን አላከማችሁትም፥ የተሰበረውን አልጠገናችሁትም፥ የባዘነውን አልመለሳችሁትም፥ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆና ገዛችኋቸው።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሙ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርባቸው፤


跟着我们:

广告


广告