Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 19:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ገዢዎች ለሚይዙት በትረ መንግሥት የሚሆኑ ብርቱ ቅርንጫፎች ነበሩአት፤ ቁመቱ ከቅርንጫፎች መካከል ረዥም ነበር፥ በርዝመቱና በቅርንጫፎቹ ብዛት ታየ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ቅርንጫፎቿ ለበትረ መንግሥት የሚሆኑ፣ ጠንካሮች ነበሩ፤ ጥቅጥቅ ባሉ ቅጠሎች መካከል፣ በቁመቷና በብዙ ቅርንጫፎቿ፣ ዘለግ ብላ፣ ጐልታ ትታይ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ቅርንጫፎቹ ብርቱዎች ስለ ነበሩ፥ በትረ መንግሥት እስከሚገኝባቸው ድረስ አደጉ፤ የወይን ተክሉም ጥቅጥቅ ካለው ደን በላይ አደገ፤ ርዝመቱ ከብዙ ቅርንጫፎች ጋር ከፍ ብሎ ታየ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከእ​ር​ስ​ዋም የጸ​ናች በትር ወጣች፤ ለገ​ዥ​ዎ​ችም በትር ሆነች፤ በዛ​ፎ​ችም መካ​ከል ቁመቷ ረዘመ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ርዝ​መቷ ታየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለእርስዋም ብርቱዎች በትሮች ነበሩአት እነርሱም ለነገሥታት በትሮች ነበሩ። ቁመታቸውም በዛፎች ቅርንጫፎች መካከል ረዘመ፥ በጫፎቻቸውም ብዛትና በርዝመታቸው ታዩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 19:11
19 交叉引用  

በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ።


በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ፥ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።


የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።


ጌታ የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፥ በጠላቶችህም መካከል ግዛ።


የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።


በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላማለች ከፊትህ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ።


ከእሴይ ግንድ ቁጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።


ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


ከቅርንጫፍዋ እሳት ወጣች፥ ፍሬዋንም በላች፥ ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆን ብርቱ ቅርንጫፍ በእርሷ ዘንድ የለም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።


እንዲገድል ተስሎአል እንዲያብረቀርቅም ተወልውሏል፥ እኛስ ደስ ይለናልን? የልጄን በትር እንደ ማንኛውም ዛፍ ንቆታል።


ፈተና ተደርጓል፥ ደግሞ የተናቀ በትር ባይኖርስ ምን ይሆናል? ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ አሦር ቅርጫፉ የተዋበ፥ ጥላ የሚሰጥ ጫካ፥ ቁመቱ የረዘመ፥ ጫፉም በቅርንጫፎች መካከል የነበረ የሊባኖስ ዝግባ ነበረ።


በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘንባባ ዝንጣፊ፥ የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በጌታ ፊት ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ።


አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤልም በትረ መንግሥት ይነሣል፥ የሞዓብንም ግንባር ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።


跟着我们:

广告


广告