Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 19:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እናትህ በደምህ፥ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለች እንደ ወይን ነበረች፥ ከውኃም ብዛት የተነሣ የምታፈራና ቅርንጫፎች የሞሉባት ነበረች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘እናትህ በውሃ አጠገብ የተተከለ፣ በዕርሻ ውስጥ ያለ፣ ከውሃም ብዛት የተነሣ፣ ያፈራና የተንሰራፋ የወይን ተክል መሰለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እናትህ በውሃ አጠገብ እንደ ተተከለች የወይን ተክል ነበረች፤ እርስዋም ከውሃው መትረፍረፍ የተነሣ በቅርንጫፎችዋና በፍሬ እንደ ተሞላች የወይን ተክል ሆነች፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “እና​ትህ በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከ​ለች እንደ ወይን ግን​ድና እንደ ጽጌ​ረዳ ነበ​ረች፤ ከው​ኃም ብዛት የተ​ነሣ የም​ታ​ፈ​ራና የም​ት​ሰፋ ሆነች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እናትህ በመልክህ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለች እንደ ወይን ግንድ ነበረች፥ ከውኃም ብዛት የተነሣ የምታፈራና የምትሰፋ ሆነች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 19:10
16 交叉引用  

እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።


በበቀለም ጊዜ ቁመቱ አጭር፥ ሐረጉ ወደ እርሱ የሚመለስ፥ ሥሮቹም በበታቹ የነበሩት ሰፊ ወይን ሆነ፥ ወይንም ሆነ፥ ቅርንጫፎችን አበቀለ፥ ቅጠልም አወጣ።


አሁንም በምድረ በዳ፥ በደረቅና በተጠማ መሬት ተተከለች።


እንዲህም በል፦ እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴት ያለች እንስት አንበሳ ነበረች! በደቦል አንበሶች መካከል ተቀምጣ ግልገሎችዋን አሳደገች።


የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።


አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ።


“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።


ጌታ አምላክህ ወደ መልካም ምድር፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች፥ ምንጮችም ወዳሉባት ምድር፥


ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያስገባሃል።


跟着我们:

广告


广告