Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በበቀለም ጊዜ ቁመቱ አጭር፥ ሐረጉ ወደ እርሱ የሚመለስ፥ ሥሮቹም በበታቹ የነበሩት ሰፊ ወይን ሆነ፥ ወይንም ሆነ፥ ቅርንጫፎችን አበቀለ፥ ቅጠልም አወጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በበቀለም ጊዜ ዐጭርና ወደ ጐን የተንሰራፋ የወይን ተክል ሆነ፤ ቅርንጫፎቹም ወደ እርሱ አቅጣጫ ዐደጉ፤ ሥሮቹ ግን እዚያው ከበታቹ ቀሩ። ስለዚህ የወይን ተክል ሆነ፤ ቅርንጫፎችን አወጣ፤ ለምለም ቅጠሎችንም አበቀለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ተክሉም አደገና ከምድር ብዙ ከፍ ሳይል በሰፊው የተንሰራፋ የወይን ተክል ሆነ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ንስሩ ከፍ ብለው አደጉ፤ ሥሮቹም ወደ መሬት ዘልቀው ገቡ፤ የወይን ተክሉ ብዙ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች አብቅሎ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በበ​ቀ​ለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ፥ ሐረ​ጉም ወደ እርሱ የሚ​መ​ለስ፥ ሥሩም በበ​ታቹ የነ​በረ ሰፊ ወይን ሆነ፤ እን​ዲሁ ወይን ሆነ፤ ሐረ​ግም ሰደደ፤ ቀን​በ​ጥም አወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በበቀለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ አረጉም ወደ እርሱ የሚመለስ ሥሩም በበታቹ የነበረ ሰፊ ወይን ሆነ፥ እንዲሁ ወይን ሆነ አረግም ሰደደ ቀንበጥም አወጣ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:6
10 交叉引用  

ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።


የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።


እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል።


ይኸውም ቃል ኪዳኑን በመጠበቅ እንድትጸና እንጂ ይህች መንግሥት እንድትዋረድና እራስዋን ከፍ እንዳታደርግ ነው።


ከምድሪቱም ዘር ወሰደ፥ በመልካም መሬትም አኖረው፥ በብዙ ውኃ አጠገብም እንደ አኻያ ዛፍ ተከለው።


ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ።


እናትህ በደምህ፥ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለች እንደ ወይን ነበረች፥ ከውኃም ብዛት የተነሣ የምታፈራና ቅርንጫፎች የሞሉባት ነበረች።


ከመንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲያ በሕዝቦች ላይ ከፍ ከፍ አትልም፤ በሕዝቦችም መካከል እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ።


ስንዴው በቅሎ ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱም ያንጊዜ ታየ።


跟着我们:

广告


广告