Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሚያመልጡ ወታደሮቹ ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ ወደ እየነፋሳቱ ይበተናሉ፥ እኔም ጌታ እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሚሸሸው ወታደሩ ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል፤ የተረፉትም ወደ ነፋስ ይበተናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ምርጥ የሆኑ ወታደሮቹ በጦር ሜዳ ይገደላሉ፤ ከሞት የሚያመልጡትም በየአቅጣጫው ይበተናሉ፤ በዚያን ጊዜ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ያመ​ለ​ጡ​ትም ሁሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቀ​ሩ​ትም ሁሉ ወደ እየ​ነ​ፋ​ሳቱ ይበ​ተ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ጭፍሮቹም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ ወደ እየነፋሳቱ ይበተናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:21
17 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤


የባቢሎን ሠራዊት ግን ንጉሥ ሴዴቅያስን እያሳደደ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ማረከው፤ ወታደሮቹም ጥለውት ሸሹ፤


አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል።


የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉት፥ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ደረሱበት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ተበትነው ነበር።


በዙሪያው ያሉ ረዳቶቹና ወታደሮቹን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፥ ከኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


ኖራ የቀባችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ፥ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይወድቃል፥ እናንተም በውስጧ ትጠፋላችሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከንቱ ራእይን አታዩም፥ ምዋርትም አታሟርቱም፥ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፥ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፥ ከአንቺም የተረፉትንም ሁሉ ወደ ሁሉም ነፋሳት እበትናለሁ።


ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር ይሞታሉ፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፥ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


ንዴቴ ያልፋል፥ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ እንዲያርፍ አደርጋለሁ፥ እጽናናለሁም፥ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ በፈጸምሁ ጊዜ እኔ ጌታ በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።


የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፥ ይህን ክፉ ነገር እንደማመጣባቸው መናገሬ በከንቱ አይደለም።


የተገደሉትም በመካከላችሁ ይወድቃሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፦ መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ ጉልላቶቹን ምታ፥ በሰዎቹም ራስ ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም።


跟着我们:

广告


广告