ሕዝቅኤል 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ ቢኖሩባትም እንኳ፣ በጽድቃቸው ራሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችን ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ እንኳ በዚያ ቢኖሩ በጽድቃቸው የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ያድናሉ እንጂ የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም”፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም በመካከልዋ ቢኖሩ፤ እኔ ሕያው ነኝ! በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |