Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስቱ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ዚህ ሦስቱ ሰዎች ኖኅና ዳን​ኤል ኢዮ​ብም በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ በጽ​ድ​ቃ​ቸው የገዛ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድ​ናሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 14:14
26 交叉引用  

ይሁን እንጂ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።


ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ።


ኖኅ፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት።


ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።


የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።


በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ከመከራቸው የተነሣ ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱም ጩኸትና ልመና አታድርግ።


ጌታም እንደዚህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ።


“እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፤ አትማልድላቸው።


እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች።


እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም።


ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም።


ወርቀዘቦ ልብሶችሽንም ወስደሽ አለበስሻቸው፥ ዘይቴንና ዕጣኔንም በፊታቸው አስቀመጥሽ።


ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ ለእነርሱ መብል እንዲሆኑ ሠዋሻቸው። አመንዝራነትሽ አንሶ ነውን?


ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች፥ ልጅ የአባትን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጅን ኃጢአት አይሸከምም፥ የጻድቅ ሰው ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የክፉ ሰው ክፋትም በራሱ ላይ ይሆናል።


እነሆ፥ አንተ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ ነህ፥ ከአንተ የተሰወረ ምሥጢር የለም።


ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው፥ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።


跟着我们:

广告


广告