Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በመከዳችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፥ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውን ነፍሳት እለቅቃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ የሕዝብን ነፍስ እንደ ወፍ በምታጠምዱበት አሸንክታብ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ከክንዳችሁ ላይ እቀዳድደዋለሁ፤ እንደ ወፍ የምታጠምዱትንም ሕዝብ ነጻ አወጣዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን የምታጠምዱባቸውን አሸን ክታቦቻችሁን እጠላለሁ፤ አሸንክታባችሁን ከጡንቻዎቻችሁ ላይ በጣጥሼ በመጣል እንደ ወፎች የምታጠምዱአቸውን ነፍሳት ነጻ አወጣለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍ​ሳ​ትን እንደ ወፍ በም​ታ​ጠ​ም​ዱ​ባት በመ​ከ​ዳ​ችሁ ላይ ነኝ፤ ከክ​ን​ዳ​ች​ሁም ወስጄ እቀ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ እንደ ወፍም የም​ታ​ጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት እለ​ቅ​ቃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በመከዳችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፥ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውን ነፍሳት እለቅቃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 13:20
6 交叉引用  

እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ ለእጅ ድጋፍ መከዳ ለሚሰፉ ለሰውም ሁሉ ራስ እንደየቁመቱ ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?


እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።


መሸፈኛዎቻችሁን ደግሞ እቀድዳለሁ፥ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚህ ወዲያ በእጃችሁ ለመታደን አይሆኑም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告