Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 13:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ቁጣዬንም በግንቡ ላይና ኖራ በቀቡት ላይ እፈጽማለሁ፥ ቅጥሩና ቅጥሩን የቀቡት የሉም እላችኋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መዓቴንም በቅጥሩና ኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ እሰድዳለሁ፤ እናንተንም እንዲህ እላችኋለሁ፤ “ቅጥሩና ቅጥሩን በኖራ የለሰኑት የሉም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “በቅጥሩ ላይና ቅጥሩን ቀለም በቀቡበት ላይ ኀይለኛ ቊጣዬን አወርዳለሁ፤ ከዚያም በኋላ ቅጥሩም ሆነ ቅጥሩን ቀለም የቀቡት አይኖሩም እላችኋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 መዓ​ቴ​ንም በግ​ንቡ ላይና ያለ​ገ​ለባ በመ​ረ​ጉት ላይ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ፤ ግን​ቡም ይወ​ድ​ቃል፤ እኔም፦ ግን​ቡና መራ​ጊ​ዎቹ የሉም እላ​ች​ኋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 መዓቴንም በግንቡ ላይ ገለባም በሌለበት ጭቃ በመረጉት ላይ እፈጽማለሁ፥ እኔም፦ ግንቡና መራጊዎቹ የሉም እላችኋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 13:15
8 交叉引用  

ወደ አምላካችን ጸለይን፥ በእነርሱም ምክንያት በሌሊትና በቀን በእነሱ ላይ ጠባቂ አቆምን።


እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።


እርሱ ብቻ ዓለቴና መድኃኒቴም ነው፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ በፍጹም አልታወክም።


ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም እዚያ ውስጥ አስገባችው፥ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።


ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።


ስለዚህ ጌታ በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት፦ ‘በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም’ ስለሚሉ ስላላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።


ኖራ የቀባችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ፥ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይወድቃል፥ እናንተም በውስጧ ትጠፋላችሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩ፥ ሰላም ሳይኖር የሰላምን ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告