ሕዝቅኤል 11:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የጌታም መንፈስ ወደቀብኝ እንዲህም አለኝ፦ ጌታ እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔ የልባችሁን ሐሳብ አውቃለሁና። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ ወረደ፤ እንዲህም አለኝ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እናንተ እንዲህ ብላችኋል፤ እኔ ግን የልባችሁን ሐሳብ ዐውቃለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ወረደ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ይህን ነገር ተናግራችኋል፤ እኔም በሐሳባችሁ ያለውን ነገር ዐውቃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህን ነገር ተናግራችኋል፤ እኔም የሰውነታችሁን በደል አውቃለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የእግዚአብሔርም መንፈስ ወደቀብኝ እንዲህም አለኝ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔም የልባችሁን አሳብ አውቃለሁ። 参见章节 |