ሕዝቅኤል 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ፥ ዘመዶችህ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ፥ “ከጌታ ራቁ፥ ምድሪቱ ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች” ብለዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ወንድሞችህ፣ የራስህ ዘመዶችና የእስራኤል ቤት ሁሉ፤ ‘ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታናለች’ ብለው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተናገሩባቸው ናቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “የሰው ልጅ ሆይ! የኢየሩሳሌም ኗሪዎች ስለ ሥጋ ዘመዶችህ፥ ስለ ተሰደዱት ወገኖችህ፥ በአጠቃላይ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ በመነጋገር ላይ ናቸው፤ ‘እነርሱ ከእግዚአብሔር ርቀው ስለ ሄዱ እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእኛ ርስት አድርጎ ሰጥቶናል’ ይላሉ”። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 “የሰው ልጅ ሆይ! በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራቁ፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች የሚሉአቸው ወንድሞችህና ዘመዶችህ፥ የምርኮ ሰዎችህም ሁሉ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ያልቃሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የሰው ልጅ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፦ ከእግዚአሔር ዘንድ ራቁ፥ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች የሚሉአቸው ወንድሞችህና ዘመዶችህ የወገኖችህም ሰዎች ሁሉ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ናቸው። 参见章节 |