ሕዝቅኤል 1:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱም ይሄዳሉ፥ የሕያዋኑ መንፈስ በመንኮራኩሮቹ ውስጥ ስለ ነበረ መንኮራኩሮቹም በእነርሱ አጠገብ ይነሡ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዳሉ፤ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ፍጥረቶቹ መንፈስ ወደሚሄድበት አቅጣጫ ሁሉ በሚበርሩበት ጊዜ፥ መንኰራኲሮቹም አብረው ይበሩ ነበር፤ ይህም የሆነው የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ ስለ ነበረ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ደመና ባለበት በዚያ መንፈስ አለ፤ እንስሶቹ ይሄዳሉ፤ ከእነርሱም ጋር መንኰራኵሮቹ ይነሣሉ፤ የሕይወት መንፈስ በመንኰራኵሮች አለና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱ ሄዱ፥ የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮቹ ውስጥ ነበረና መንኰራኵሮቹ በእነርሱ አጠገብ ከፍ ከፍ አሉ። 参见章节 |