Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጀርባቸውም ረዥምና የሚያስፈራ ነበር፥ የአራቱም ጀርባቸው ዙሪያው በዐይኖች ተሞልቶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የመንኰራኵሮቹ ክብ ጠርዝ ረዥምና አስፈሪ ነበር፤ የአራቱም መንኰራኵሮች ክብ ጠርዝ ዙሪያውን በዐይኖች የተሞላ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የመንኰራኲሮቹም ጠርዝ ግዙፍና የሚያስፈራ ነበር፤ አራቱም የመንኰራኲር ጠርዝ ዙሪያቸውን በዐይን የተሞሉ ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በአ​ራቱ ዙሪያ ሁሉ ዐይ​ኖ​ችን የተ​መላ ጀር​ባ​ቸ​ውን አየሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ቁመታቸውም የረዘመና የሚያስፈራ ነበረ፥ የአራቱም ክበብ ዙሪያው በዓይን ተሞልቶ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:18
10 交叉引用  

መንኰራኲሮቹም የሠረገላ መንኰራኲሮችን ይመስሉ ነበር፤ ወስከምቶቻቸው፥ ቅትርቶቻቸውና ዐቃፊዎቻቸው ሁሉም ከነሐስ ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።


የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።


ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።


መላ አካላቸው ሁሉ፥ ጀርባቸው፥ እጃቸው፥ ክንፋቸው፥ መንኰራኵሮቹም፥ የአራቱም መንኰራኵሮች፥ ዙሪያቸው በሙሉ በዐይኖች ተሞልተው ነበር።


የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”


በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።


አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።


跟着我们:

广告


广告