Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የፊታቸውም ምስል የሰው ፊት፥ አራቱም በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፥ በግራ በኩል የላም ፊት ነበራቸው፥ አራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፊታቸውም እንዲህ ነበር፤ አራቱም እያንዳንዳቸው የሰው ፊት ነበራቸው፤ በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፣ በግራ በኩልም የበሬ ፊት ነበራቸው፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እያንዳንዱ ፍጥረት አራት የተለያዩ ፊቶች ነበሩት፤ ይኸውም ከፊት ለፊት የሰው መልክ የሚመስል፥ በስተቀኝ በኩል የአንበሳ መልክ፥ በስተግራ የበሬ ፊት፥ በስተ ኋላም የንስር መልክ የሚመስል ነበሩት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የፊ​ታ​ቸው አም​ሳያ እን​ደ​ዚህ ነው፦ ለአ​ራቱ ሁሉ በቀ​ኛ​ቸው የሰው ፊትና የአ​ን​በሳ ፊት አላ​ቸው፤ ለአ​ራ​ቱም ሁሉ በግ​ራ​ቸው የእ​ን​ስሳ ፊትና የን​ስር ፊት አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የፊታቸው አምሳያ እንደ ሰው ፊት ነበረ፥ ለአራቱም በስተ ቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተ ግራቸውም እንደ ላም ፊት ነበራቸው፥ ለአራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:10
20 交叉引用  

ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአምባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ በጋሻና በጦር ስልታቸው የተካኑ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ተዋጊዎች፥ ወደ እርሱ መጡ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።


ንስር ከፍ ከፍ የሚለው፥ ቤቱንም በከፍታ ላይ የሚያደርገው በአንተ ተእዛዝ ነውን?


በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም፥ ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው።


ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


ይህን አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ።


እያንዳንዳቸውም አራት ፊቶች፥ እያንዳንዳቸውም አራት ክንፎች ነበራቸው።


እያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፥ ሦስተኛው ፊት የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም ፊት የንስር ፊት ነበረ።


የሰው ፊት በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት ደግሞ በሌላው ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እንደዚህ ተቀርጾ ነበር።


“በደቡብ በኩል በየሠራዊቶቻቸው የሮቤል ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የሮቤልም ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበረ።


“በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ።


“በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ።


በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳን ሰፈር ዓላማ የያዙት ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።


እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”


ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁ ግን ጐልማሶች ሁኑ።


ጌታ እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋው የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤


ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበር ንስር ይመስል ነበር።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፥ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፥ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፥ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው።


跟着我们:

广告


广告