Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ፈርዖንም እረፍት እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጓጕንቸሮቹም ከአንተና ከቤቶችህ፣ ከሹማምትህና ከሕዝብህ ተወግደው በአባይ ወንዝ ብቻ ይወሰናሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጓጕንቸሮቹም ከአንተ፥ ከቤቶችህም፥ ከባርያዎችህም፥ ከሕዝብህም ይሄዳሉ፤ በወንዙም ብቻ ይቀራሉ” አለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:11
7 交叉引用  

ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።


ልክ ጌታ እንደ ተናገረው የፈርዖን ልብ ጸና፥ አልሰማቸውምም።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቅም አለ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ዘርጋ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ ተናካሽ ትንኝ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው።’”


እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ።


አስማተኞችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አወጡ።


ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ።


跟着我们:

广告


广告