Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነዚህ የሌዊ ልጆች ስሞች እንደ ትውልዳቸው ጌርሾን፥ ቀሃት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制




ዘፀአት 6:16
22 交叉引用  

የይስሐቅም ዕድሜ መቶ ሰማንያ ዓመት ሆነ።


የሌዊም ልጆች፥ ጌድሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


የሮቤልም ልጆች፥ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ካርሚ።


ያዕቆብም በግብጽ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ፥ የያዕቆብም የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነው።


ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፤ በሽቶም አሹት፥ በግብጽ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።


ዳዊትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድሶንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራሪም በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ።


ሌዋውያኑም፥ ከቀዓት ልጆች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፥ ከሜራሪም ልጆች የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፥


ከሌዊ ወገን የሆነ አንድ ሰው ሄዶ የሌዊን ልጅ አገባ።


የቀሃትም ልጆች ዓምራም፥ ይፅሃር፥ ሔብሮን፥ ዑዚኤል ናቸው፤ የቀሃትም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።


ዓምራምም የአባቱን እኅት ዮካቤድን አገባ፥ አሮንንና ሙሴንም ወለደችለት፤ የዓምራምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ የኤልያብ ልጆች ዳታንንና አቤሮንን ከሮቤልም ልጆች የፋሌት ልጅ ኦንን ወሰዳቸው።


ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።


በየስማቸውም የሌዊ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


የጌድሶንም ልጆች ስሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ሎቤኒ፥ ሰሜኢ።


የቀዓትም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል።


የሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።


በጌድሶን ውስጥ የሎቤናውያን ወገንና የሰሜአውያን ወገን ይካተቱ ነበር፤ የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።


ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።


ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


跟着我们:

广告


广告