Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሆኖም ቀድሞ በሚያቀርቡት ሸክላ ልክ ሠርተው እንዲያቀርቡ አድርጓቸው። የሥራ ድርሻቸውን አትቀንሱ። ሰነፎች ናቸው፤ ‘ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት እንሠዋ’ የሚሉትም ለዚህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 5:8
6 交叉引用  

በአሕዛብም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።


በብርቱ ሥራ እንዲያስጨንቁአቸው ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራዓምሴስን የማከማቻ ከተሞች አድርገው ሠሩ።


እርሱም አላቸው፦ “ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለጌታም እንሠዋ’ ትላላችሁ።


የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጉድሉ” በተባሉ ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ።


“እንደ ቀድሞው ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ሄደው ገለባ ይሰብስቡ።


ሥራውን እንዲሰሩት፥ የሃሰትን ቃላት እንዳያስቡ፥ በሰዎቹ ላይ ሥራው ይክበድባቸው።”


跟着我们:

广告


广告