Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነርሱም፦ “ጌታ እናንተ ላይ ይፍረድባችሁ፥ ሽታችንን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አግምታችሁታልና፥ እንዲገድሉንም ሰይፍን በእጃቸው አስቀምጣችኋዋልና” አሉአቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤ ፈርዖንና ሹማምቱ እንዲጠየፉን አደረጋችሁ፤ እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ሰጣችኋቸው” አሏቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሙሴንና አሮንንም “በንጉሡ በፈርዖንና በመኳንንቱ ዘንድ እጅግ እንድንጠላ በማድረጋችሁና በሰይፍ ይገድሉንም ዘንድ ምክንያት በመሆናችሁ፥ እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ እርሱም ይፍረድባችሁ፤” አሉአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 5:21
19 交叉引用  

ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን፥ እኔ ባርያዬን በጉያህ ሰጠሁህ፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ፥ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው።


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ “በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ፥ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፥ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል፥ እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።”


አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራም-መዓካ፥ ከሱባ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።


ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “በግብጽ መቃብር ስለ ሌለ ነው በምድረ በዳ እንድንሞት ያወጣኸን? ከግብጽ አውጥተህ ምንድነው ያደረግህብን?


ሕዝቡም፦ “ምን እንጠጣለን?” ብለው በሙሴ ላይ አጉረመረሙ።


የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በምድረ በዳ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ።


ሕዝቡም አመኑ፤ ጌታ የእስራኤልን ልጆች እንደተመለከተ ጭንቀታቸውንም እንዳየ በሰሙ ጊዜ፥ አጎነበሱ ሰገዱም።


ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን ቆመው አገኙአቸው።


ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ እነርሱ ግን ከመንፈሳቸው መሰበር ከከባዱም ሥራ የተነሣ ሙሴን አልሰሙትም።


የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፥ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።


በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥


ጌታም በሰይፍ እንድንሞት ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ለምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”


እስራኤላውያን ሁሉ፥ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የተጠሉ ሆኑ” የሚለውን ወሬ ሰሙ። ሕዝቡም ከሳኦል ጋር ለመሰለፍ ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።


አኪሽም በልቡ፥ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፥ ለዘለዓለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።


跟着我们:

广告


广告