Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 36:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 አራት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች ሠራላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ለርሱም አራት ምሰሶዎች ከግራር ዕንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጧቸው፤ ለእነርሱም አራት የወርቅ ኵላቦችንና አራት የብር መቆሚያዎችን አበጁላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 መጋረጃዎቹን የሚያያይዙ አራት ምሰሶዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸውንም ከወርቅ ሠሩ፤ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን አራት እግሮችንም ከብር ሠሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት አራት ምሰ​ሶ​ዎች አደ​ረ​ጉ​ለት፤በወ​ር​ቅም ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ርቅ ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አራት የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከግራርም እንጨት አራት ምሰሶች አደረጉለት፥ በወርቅም ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 36:36
5 交叉引用  

ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፥


“መጋረጃውንም ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ።


መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ሠራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረገ።


ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ መጋረጃ አደረገ፤


እነሆ እኔም፥ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ የተመሸገ ከተማ፥ የብረትም ዓምድ፥ የናስም ቅጥሮች ዛሬ አድርጌሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告