Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 36:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የመቅደሱን ሥራ ለመሥራት የእስራኤል ልጆች ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ወሰዱ። እነዚያም በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ስጦታ አሁንም ማለዳ ማለዳ ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የመቅደሱን የግንባታ ሥራ ለማከናወን እስራኤላውያን ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ፤ ሕዝቡ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎችን በየማለዳው ማምጣታቸውን ቀጠሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱም እስራኤላውያን ለተቀደሰው ድንኳን መሥሪያ እንዲውል ያመጡትን ስጦታ ከሙሴ እጅ ተቀበሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን በየማለዳው ስጦታቸውን ለሙሴ ከማምጣት አልተቈጠቡም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለመ​ቅ​ደስ ማገ​ል​ገያ ሥራ ያመ​ጡ​ትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀ​በሉ። እነ​ዚ​ያም እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው ማለዳ ማለዳ ስጦ​ታ​ውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

参见章节 复制




ዘፀአት 36:3
11 交叉引用  

ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥ የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ።


የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።


አለቆችም የመረግድ ድንጋይ፥ በኤፉድና በደረት ኪስ የሚገቡ ፈርጦችን፥


ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።


ሙሴም ባስልኤልን፥ ኤልያብንና ጌታ በልቡ ጥበብን ያሳደረበትን ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውን ሁሉ ጠራቸው።


የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፥


ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥ ሹማምንትም የቀናውን ነገር ይደነግጋሉ።


የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።


የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’


እርሾም ያለበትን የምስጋናውን መሥዋዕት አቅርቡ፥ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告