Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጐ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠረበ፤ በማግስቱም ማልዶ ጌታ እንዳዘዘው ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ሙሴ እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጠርቦ፣ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማለዳ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላትም በእጆቹ ያዘ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህ ሙሴ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ልክ እንደ ፊተኞቹ ቀረጸ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ጽላቶቹን ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሙሴም እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ርጎ ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለ​ቱ​ንም የድ​ን​ጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነ​ጋ​ውም ማልዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጐ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረበ፤ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፥ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ወሰደ፥

参见章节 复制




ዘፀአት 34:4
6 交叉引用  

ጌታ በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራራው ራስ ወረደ፤ ጌታ ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።


ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ወጣ፤ ጌታም ከተራራው ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ለያዕቆብ ቤት እንዲህ በል፥ ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ንገር፦


ጽላቶቹ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፥ በጽላቶቹ ላይ የተቀረው ጽሑፍም የእግዚአብሔር ጽሑፍ ነበረ።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ፥ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።


በዚያን ጊዜ ጌታ እንዲህ አለኝ፥ “እንደ ቀድሞ ዓይነት ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ።


“እኔም ከግራር እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ቀድሞዎቹም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፥ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።


跟着我们:

广告


广告