ዘፀአት 30:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙ፣ ከክፈፉ በታች ትይዩ የሆኑ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ለመሠዊያው አብጅ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጐን ታደርጋቸዋለህ፤ እርሱን ያነሡባቸው ዘንድ የመሎጊያዎቹ መግቢያ ይሁኑ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ። 参见章节 |