Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 30:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከርሱም ጥቂቱን ወቅጠህ ዱቄት በማድረግ አልመህ በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ፊት ለፊት ከአንተ ጋራ በምገናኝበት ስፍራ አስቀምጠው፤ ለአንተ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከእ​ር​ሱም ጥቂት ትወ​ቅ​ጣ​ለህ፤ ታል​መ​ው​ማ​ለህ፤ ከዚ​ያም ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታልመውማለህ፤ ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 30:36
7 交叉引用  

ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተጠብቆ እንዲኖር አሮን በምስክሩ ፊት አስቀምጠው።


በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች እንድታዝዝ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።


ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”


ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ።


በምስክሩ ታቦት አጠገብ ካለው መጋረጃ ፊት ታኖረዋለህ፥ ለአንተ በምገለጥበት ከምስክሩ በላይ ባለው በስርየት መክደኛ ፊት ታኖረዋለህ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።


跟着我们:

广告


广告