Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 30:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱ የተሠራ ሌላ ቅባት አትስሩ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በማንም ሰው ሰውነት ላይ አታፍስሱት፤ በተመሳሳይ መንገድ ምንም ዘይት አትሥሩ፤ የተቀደሰ ነው፤ ቅዱስ መሆኑን ልብ በሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በማንኛውም ተራ ሰው ላይ አይፍሰስ፤ ይህንንም የመሰለ ቅባት ለመሥራት በዚህ ዘዴ ከመጠቀም ተጠንቀቁ፤ ቅዱስ ስለ ሆነ እናንተም ቅድስናውን ዕወቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በሌላ ሰው ሥጋ ላይ አይ​ፍ​ሰስ፤ እንደ እር​ሱም የተ​ሠራ ሌላ ቅብ​ዐት አታ​ድ​ርጉ፤ ቅዱስ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም ቅዱስ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱም የተሰራ ሌላ ቅብዓት አታድርጉ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን።

参见章节 复制




ዘፀአት 30:32
5 交叉引用  

በቀማሚ እንደሚቀመም ቅመም የተቀደሰ የቅባት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅባት ዘይትም ይሆናል።


የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ለእኔ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ነው።


“በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


跟着我们:

广告


广告