Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሮንንና ልጆቹን በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብን ታለብሳቸዋለህ፤ ክህነትም ለዘለዓለም ለእነርሱ የተወሰነ ይሆናል፥ እንዲሁም አሮንን እጅና የልጆቹን እጅ ትቀድሳለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የራስ ማሰሪያዎችንም አድርግላቸው፤ ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መታጠቂያዎችን አስታጥቃቸው፤ ክህነት የዘላለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል። “በዚህም መንገድ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትክናቸዋለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለወገባቸውም መታጠቂያ አድርግላቸው፤ በራሳቸውም ላይ ቆብ ድፋላቸው፤ ክህነታቸው ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ በዚህም ዐይነት አሮንንና ልጆቹን ትሾማለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አሮንንና ልጆቹንም በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብንም ታለብሳቸዋለህ፤ ለዘላለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም አሮንንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:9
22 交叉引用  

ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”


ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።


ሙሴም “ዛሬ በላያችሁ ላይ በረከት እንዲያወርድ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ ተነሥቷልና ዛሬ ለጌታ እጃችሁን ቀደሳችሁ” አለ።


አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፥ ካህናትም ይሆኑልኛል፤ ቅባታቸውም ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለዘለዓለም ክህነት ይሆንላቸዋል።”


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመርገፍም በተጌጠ መታጠቂያ አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው።


እናንተን በቅድስና ማዕረግ ለመሾም ሰባት ቀን ይወስዳልና የክህነታችሁ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ሰባት ቀን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።


አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ፈቅዶላችኋል፤ ታዲያ አሁን ደግሞ ክህነትንም ትፈልጋላችሁን?


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።


በቆሬና በእርሱም ተከታዮች ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በጌታ ፊት ዕጣንን ለማጠን እንዳይቀርብ፥ ጌታ በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።


አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”


ለአምላኩም ቀንቶአልና፥ ለእስራኤልም ልጆች አስተስርዮአልና ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም የክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል።’ ”


አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።”


በጌታ ስም ቆሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።


በእግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ተጠራ።


ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።


跟着我们:

广告


广告