Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የዘወትር የእስራኤላውያን ድርሻ የሚሆነው ይህ ነው፤ ከኅብረት መሥዋዕታቸው እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሕዝቤ የአንድነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የእንስሳው ፍርምባና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ ሆኖ እንዲመደብ ወስኛለሁ፤ ውሳኔውም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ ይህ እንግዲህ ሕዝቡ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው መባ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይህም የተ​ለየ ቍር​ባን ነውና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ል​ጆች ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ያውም የማንሣት ቍርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ለዘላለም የአሮንና የልጆቹ ወግ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የማንሣት ቍርባን ይሆናል፤ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን ይሆናል።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:28
18 交叉引用  

ለክብርና ለውበት እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን የተቀደሰ ልብስ ሥራለት።


ለክህነት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።


የተቀደሰው የአሮን ልብስ ከእርሱ በኋላ ለልጆቹ ይሁን፥ ይኸውም እንዲቀቡበትና ክህነትን እንዲቀበሉበት ነው።


“ቁርባኑም የአንድነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከበሬ መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በጌታ ፊት ያቅርብ።


መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ እንደ ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቡትን ቁርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለጌታ ትሰጣላችሁ።


ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን የሚያቀርቡትን የእስራኤልን ልጆች አሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህ፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም አልኋቸው።”


የእናንተ ከሆነው ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከእርሱም ከተቀደሰው ድርሻ ሁሉ፥ የጌታን የስጦታ ቁርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ።’


ጌታም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የቀደሱትን እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባኔን ሁሉ ለአንተ እንድትጠብቀው ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተና ለልጆችህ የክህነትህ ድርሻ እንዲሆን ለአንተ የተገባህ አድርጌ ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ።


ሙሴም አሮን የለበሰውን ልብስ አወለቀ፥ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ።


ከድርሻቸው ወስደህ ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን አግርህ ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለጌታ የስጦታ ቁርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።


የማናቸውም ሰው የተቀደሱ ነገረሮች ለራሱ ለሰውዬው ይሆናሉ፤ ማናቸውም ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ሁሉ ግን ለካህኑ ይሆናል።”


የእስራኤልም ልጆች ለካህኑ የሚያቀርቡትን ማናቸውም የተቀደሱ ነገሮች ስጦታ ሁሉ ለእርሱ ይሆናሉ።


ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል።


“በሬ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ አገጩንናና ሆድ ዕቃውን ነው።


跟着我们:

广告


广告