Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ለክህነት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ለክህነት የሆኑትን የአውራውን በግ ብልቶች ቀድሳቸው። የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:27
14 交叉引用  

ለአሮን የክህነት ሥርዓት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል።


የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።


የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ከሆነው ስብ ጋር ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት እንዲወዘወዝ ያመጣሉ፤ ጌታ እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ላሉት ለልጆችህ የዘለዓለም ድርሻ ይሆናል።”


የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።


የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።


ሙሴም እንደ ታዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘ።


ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው።


ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል።


“በሬ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ አገጩንናና ሆድ ዕቃውን ነው።


ሕጉ ሰዎችን ድካም እያላቸው ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማል፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን፥ ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾመልን።


ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፥ “ይህ፥ እንግዶችን ጋብዣለሁ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ፥ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።


跟着我们:

广告


广告