Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ላይ ታኖረዋለህ፤ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እነዚህን ሁሉ በአሮንና በወንዶች ልጆቹ እጆች ላይ በማኖር እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዛቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ይህን ሁሉ ምግብ በአሮንና በልጆቹ እጅ ላይ አኑር፤ እርሱንም ወዝውዘው ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታኖረዋለህ፤ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:24
9 交叉引用  

አንድ ክብ ዳቦ፥ አንድ በዘይት የተለወሰ እንጎቻ፥ አንድ ስስ ቂጣ በጌታ ፊት ካለው ያልቦካ ቂጣ ማስቀመጫ ሌማት ትወስዳለህ፤


ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በጌታ ፊት መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ታቃጥለዋለህ፤ ይህም ለጌታ የእሳት ቁርባን ነው።


ነገር ግን የሚወዘወዘውን ፍርምባ፥ የሚነሣውንም ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህና ሴቶች ልጆችህም በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ፤ እነዚህ ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕት ለአንተና ለልጆችህ ድርሻ እንዲሆኑ የተሰጡ ናቸውና።


እርሱም ነዶውን በጌታ ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ ካህኑ የሚወዘውዘው በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ነው።


የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።


ሁሉንም በአሮንና በልጆቹ እጆች ላይ አደረገ፥ በጌታም ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዛቸው።


ሙሴም እንደ ታዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘ።


“ካነጻሓቸውና ለመወዝወዝም ቁርባን ካቀረብካቸው በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ።


跟着我们:

广告


广告