ዘፀአት 29:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 አንድ ክብ ዳቦ፥ አንድ በዘይት የተለወሰ እንጎቻ፥ አንድ ስስ ቂጣ በጌታ ፊት ካለው ያልቦካ ቂጣ ማስቀመጫ ሌማት ትወስዳለህ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በእግዚአብሔር ፊት በሌማት ካለው ያለ እርሾ ከተጋገረው ቂጣ፣ ዳቦ፣ በዘይት የተሠራ ዕንጐቻና ኅብስት ውሰድ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 በመሶብ ሆኖ ለእኔ ለእግዚአብሔር ከቀረበው ቂጣ ከየአንዳንዱ ዐይነት አንድ ሙልሙል ውሰድ፤ ይኸውም ዘይት ተጨምሮበት ከተጋገረው አንድ፥ ዘይት ካልገባበትም አንድ፥ እንዲሁም ሌላ አንድ ስስ ቂጣ ጨምረህ ትወስዳለህ ማለት ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በእግዚአብሔር ፊት በመሶብ ካለው አንድ የዘይት እንጀራና አንድ የቂጣ እንጐቻ ትወስዳለህ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 አንድ እንጀራ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ በእግዚአብሔር ፊት በሌማት ካለው ቂጣ እንጀራ ትወስዳለህ፤ 参见章节 |