Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅባት ዘይት ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱና ልብሶቹ፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹና ልብሶቻቸው ይቀደሳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅብዐ ዘይቱ ወስደህ በአሮንና በልብሶቹ ላይ እንዲሁም በወንዶች ልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ርጨው። ከዚያም እርሱና ወንዶች ልጆቹ እንዲሁም ልብሶቻቸው የተቀደሱ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በመሠዊያው ላይ ካለው ደም ጥቂት፥ ከቅባቱም ዘይት ጥቂት ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ በአሮን ልጆችና በልብሶቻቸው ላይ ርጨው፤ በዚህ ዐይነት እርሱና ልጆቹ ከነልብሶቻቸው ለእኔ የተለዩ ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ካለው ደም ከቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም ወስ​ደህ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባሉት በል​ጆ​ቹና በል​ብ​ሶ​ቻ​ቸው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ልብ​ሶ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ደ​ሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በመሠዊያውም ላይ ካለው ደም ከቅብዓት ዘይትም ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር ባሉት በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱም ልብሶቹም፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹ ልብሶቻቸውም ይቀደሳሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:21
16 交叉引用  

ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም እንደሚፈስስ፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።


“ለእኔ ካህናት እንዲሆኑ እንድትቀድሳቸው የምታደርገው ነገር ይህ ነው፤ አንድ ወይፈንና ነውር የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ።


አውራውን በግ አርደህ ደሙን ትወስዳለህ፥ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ትረጨዋለህ።


ለክህነት ሥርዓት የቀረበ አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶቹ፥ በላያቸውም ያለውን ስብና የቀኙን ወርች ትወስዳለህ።


የቅባትን ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባዋለህም።


በጌታ ፊት እንዲያስተሰርይለት ካህኑ በእጁ መዳፍ ላይ የተረፈውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርገዋል።


“ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው።


አረደውም፤ ሙሴም ከደሙ ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት አስነካው።


ሙሴም ከቅባቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።


እነርሱም ደግሞ በእውነትህ የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።”


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?


እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፤ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።


跟着我们:

广告


广告