Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑም አንድ ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የተቀደሰው ድንኳን አንድ ይሆን ዘንድ ለእነዚህ ሁለት ክፍሎች ኀምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሠርተህ በቀለበቶቹ አገጣጥማቸው።።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ ማደሪያውንም አንድ እንዲሆን መጋረጆችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 26:6
11 交叉引用  

አምሳ የናስ መያዣዎችን ሥራ፥ መያዣዎቹንም ወደ ቀለበቶቹ አስገባቸው፥ ድንኳኑንም አጋጥመው።


መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።


አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት እንዲሆኑ አድርግ።


ከማደሪያውም በላይ ለመሸፈኛ የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር ሥራ፤ ዐሥራ አንድ መጋረጆች ትሠራለህ።


ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቃዎቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፤


አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሠራ፤ መጋረጆችንም እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጠማቸው፤ ማደሪያውም አንድ ወጥ ሆነ።


ድንኳኑ አንድ ወጥ እንዲሆን የሚያጋጥሙበት አምሳ የነሐስ መያዣዎችን ሠራ።


ማደሪያውን ወደ ሙሴ አመጡት፥ ድንኳኑን፥ የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶቹንና እግሮቹን፥


ከእርሱም የተነሣ መላው አካል በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።


跟着我们:

广告


广告