Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ፀሐይ ከወጣችበት ግን ደሙ በላዩ ነው፥ ዋጋውን ይክፈል፤ የሚከፍለው ከሌለው ስለ ሰረቀው ነገር ይሸጥ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “አንድ ሌባ በር ሲሰብር ተይዞ ቢደበደብና ቢሞት፣ ተከላካዩ የደም ባለዕዳ አይሆንም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2-3 ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለው ቢያጣ በባሪያነት ይሸጥ፤ የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት በእጁ ቢገኝ ለያንዳንዱ እንስሳ እጥፍ ዋጋ ይክፈል። “አንድ ሌባ ቤት ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመትቶ ቢገደል ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ አይሆንም። ሌባው ሰብሮ የገባው ፀሐይ ከወጣ በኋላ ሆኖ ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሌባ ቤት ሲምስ ቢገኝ፥ እር​ሱም ቢመታ፥ ቢሞ​ትም በመ​ታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይ​ሆ​ን​በ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሌባው ቤት ሲምስ ቢገኝ፥ እርሱም እስኪሞት ቢመታ፥ በመታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይሆንበትም።

参见章节 复制




ዘፀአት 22:2
11 交叉引用  

ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል፥ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፥ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።


ቤቶቹን በጨለማ ይሰረስራሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም።


ከሰዎች ተለይተው ተሰደዱ፥ በሌባ ላይ እንደሚጮኽ ይጮኹባቸዋል።


እንዲሁም ሲምሱ አልያዝሻቸውም ነገር ግን በልብሶችሽ ላይ የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብትፈጽሚም እንኳ


በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በገላጣም ስፍራ ወንበዴ ቀምቶአልና፤ እስራኤልን በፈወስሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።


በከተማም ያኰበኩባሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፥ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።


ደም ተበቃዩም ከመማፀኛው ከተማ ድንበር ውጭ ቢያገኘው፥ ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ቢገድለው፥ የደም ዕዳ አይሆንበትም፤


“ነገር ግን ይህን እወቁ፤ ባለቤት ሌባ ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ ነቅቶ በጠበቀ ነበር፤ ቤቱም እንዲቆፈር ባልተወም ነበር።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።


跟着我们:

广告


广告