Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 20:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከእኔ ጋር የብር አማልክትን አትሥሩ፥ የወርቅ አማልክትንም ለእናንተ አትሥሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሯችሁ፤ ከብር ወይም ከወርቅ ለእናንተ አማልክትን አታብጁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እኔን ብቻ አምልኩ እንጂ፥ ከብርና ከወርቅ ጣዖቶች ሠርታችሁ አታምልኩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የብር አማ​ል​ክ​ትን አታ​ም​ልኩ፤ የወ​ርቅ አማ​ል​ክ​ት​ንም አታ​ም​ልኩ። የዕ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አም​ላ​ክ​ንም አታ​ም​ልኩ፤ እን​ዲህ ያለ አም​ላ​ክን ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በአጠገቤ ምንም አታድርጉ፤ የብር አማልክት የወርቅም አማልክት ለእናንተ አታድርጉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 20:23
21 交叉引用  

በዚህም ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክታቸው ይሰግዱ ነበር።


እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።


ሙሴም ወደ ጌታ ተመልሶ “ወዮ! እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል፥ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል፤


ቀልጠው የተሠሩ የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።


መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውን በመቃኔ አጠገብ በማድረጋቸው፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ቀረ፥ በሠሩት ርኩሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፥ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።


ወደ ጣዖታትም ዘወር አትበሉ፥ ለራሳችሁም ይሆኑ ዘንድ ቀልጠው የተበጁትን የአማልክት ምስሎች አትሥሩ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


በሰገነትም ላይ ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ ለጌታ የሚሰግዱትንና በእርሱም የሚምሉትን፥ በንጉሣቸውም ደግሞ የሚምሉትን፥


“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


በመካከላቸውም አስጸያፊ ምስሎቻቸውንና የዕንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል።


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።


跟着我们:

广告


广告