Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 20:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሕዝቡም መብረቁንና ነጐድጓዱን የተራራውን መጤስና የመለከቱን ድምፅ ባዩና በሰሙ ጊዜ በፍርሀት ተንቀጠቀጡ፤ በርቀትም ቆሙ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ።

参见章节 复制




ዘፀአት 20:18
13 交叉引用  

ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፥ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።


እርሱም፥ “በገነት ድምጽህን ሰማሁ፥ ዕራቁቴንም ስለ ሆንኩ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።” አለ።


ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


እኔ የቅርብ አምላክ ነኝን? ይላል ጌታ፥ የሩቅስ አምላክ አይደለሁምን?


በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና።


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ሁሉ፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፥


ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና፥ እንግዲያውስ አሁን ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የጌታን ድምፅ ደግመን ከሰማን እንሞታለን።


አንተ ቅረብ፤ አምላካችን ጌታ የሚለውን ሁሉ ስማ፤ አምላካችን ጌታም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።’


እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችሁ፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና፤ በዚያን ጊዜ፥ እኔ የጌታን ቃል ልነግራችሁ፥ በጌታና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦


跟着我们:

广告


广告