Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 19:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገን ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ሕዝቡ ሂድና ዛሬና ነገ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውን እንዲያጥቡ አድርግ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፥ “ወደ ሰዎቹ ሂድ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ አድርገህ ታቀርባቸው ዘንድ ዛሬና ነገ ሰውነታቸውን እንዲያነጹና ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ ንገራቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገም ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤

参见章节 复制




ዘፀአት 19:10
24 交叉引用  

ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥


ስለዚህ ንጉሡ ሺምዒን፥ “አትሞትም” አለው፤ ይህንንም ንጉሡ በመሐላ አጸናለት።


ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ ጥቂቶች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር።


እንዲህም አላቸው፦ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የጌታን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።


የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።


በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ሕዝቡንም እንዲህ በላቸው፦ ለነገ ተቀደሱ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ ምክንያቱም እንዲህ እያላችሁ ያለቀሳችሁት ለቅሶ ወደ ጌታ ጆሮ ደርሶአልና፦ ‘የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብጽ ሳለን በዚያ ደኅና ነበርን፤’ ስለዚህ ጌታ ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበላላችሁም።


ንጹሑም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ርኩስ በሆነው ሰው ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ያነጻዋል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በመሸም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።


በእሳት ለማለፍ የሚችለውን ሁሉ በእሳት ታሳልፉታላችሁ፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ።


በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን ታጥባላችሁ፥ ንጹሕም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትገባላችሁ።”


ሌዋውያንም ከኃጢአት ራሳቸውን አነጹ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም እነርሱን ለማንጻት ማስተስረያ አደረገላቸው።


እነርሱንም ለማንጻት እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ላይ ያለውን ጠጉር ሁሉ በምላጭ ይላጩ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ራሳቸውንም ንጹሕ ያድርጉ።


ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


ኢያሱም ሕዝቡን፦ “ነገ ጌታ በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ” አለ።


ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስከ ነገ ተቀደሱ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፦ “እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።”


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፥ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።


ሳሙኤልም፥ “አዎን፤ ለሰላም ነው፤ የመጣሁትም ለጌታ መሥዋዕት ላቀርብ ነው፤ እናንተም ራሳችሁን ቀድሳችሁ ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ” ሲል መለሰላቸው። ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም እንዲመጡ ጠራቸው።


跟着我们:

广告


广告