Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሙሴ አማትም ለሕዝቡ ያደርግ የነበረውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ “ለሕዝቡ የምታደርገው ይሄ ነገር ምንድነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመዋል፥ አንተ ብቻህን ለምን ተቀምጠሃል?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዐማቱም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከጧት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመው ሳለ፣ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የሙሴ ዐማት የትሮም ለሕዝቡ ያደርገው የነበረውን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ሁሉ ለሕዝቡ የምታደርገው ነገር ምንድን ነው? ሕዝቡ አንተን ለማነጋገር በመፈለግ ከጠዋት እስከ ማታ በዙሪያህ በመቆም እንደዚህ የሚያጨናንቅህና አንተም ይህን ሁሉ ጉዳይ በዳኝነት ለማየት ብቻህን የምትቀመጠው ለምንድነው?”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዮቶ​ርም ሙሴ በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አይቶ እን​ዲህ አለው፥ “ብቻ​ህን ተቀ​ም​ጠህ በሕ​ዝቡ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ምን​ድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥ​ዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙ​ሪ​ያህ ቆመ​ዋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሙሴም አማት በሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ ይህ በሕዝቡ የምታደርገው ምንድር ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመው ሳሉ አንተ ብቻህን ስለ ምን ተቀምጠሃል? አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 18:14
6 交叉引用  

አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል።


በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።


ሙሴም አማቱን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤


በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፥ ትንሹን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ።


በእርሱም ላይ ምን ሊደረግበት እንደሚገባ ገና ግልጽ አልነበረምና በእስር ቤት አኖሩት።


የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።


跟着我们:

广告


广告