ዘፀአት 16:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ከኤሊምም ተነሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር፥ በዓሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከኤሎም ተጓዙ፤ ከግብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በኤሎምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከኤሊምም ተጓዙ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብፅ አገር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። 参见章节 |