Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 14:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታም በዚያን ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤልም የግብፃውያንን ሞት በባሕር ዳር አዩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 በዚያች ዕለት እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጻውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም የግብጻውያን ሬሳ በባሕሩ ዳርቻ ወድቆ ተመለከቱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 በዚያን ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብጻውያን እጅ አዳናቸው፤ በባሕር ሸሸ የተረፈረፈውንም የግብጻውያንን ሬሳ ተመለከቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅ አዳ​ና​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሞቱ በባ​ሕር ዳር አዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን እንደዚህ ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤልም የግብፃውያንን ሬሳ በባሕር ዳር አዩ።

参见章节 复制




ዘፀአት 14:30
17 交叉引用  

እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።


ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።


ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ አዳናቸው።


ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።


እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።


በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።


ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፥ ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና።


እርሱም የቀደመውን ዘመን እንዲህ ብሎ አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለው? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለው?


እርሱም፦ “በእውነት ሕዝቤ፥ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፥ ናቸው” አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው።


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።”


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።


ጌታም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብፃውያን፥ አሞራውያን፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥


ሳኦል ግን፥ “ይህ ዕለት ጌታ እስራኤልን የታደገበት ቀን ሰለሆነ፥ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ።


በዚያ ቀን ጌታ እስራኤልን ታደገው፤ ጦርነቱም ከቤትአዌን ዘልቆ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告